የሚዲያ ግንዛቤ (Media Literacy) Part III

የሚዲያ ግንዛቤ መርሆች

  1. ሁሉም ሚዲያዎች የተፈበረኲ ናቸው

በሚዲያ የሚቀርብ ማንኛውም ሐሳብ እውነትን ለማሳየት የተጠቀሙበት ዘዴ እንጂ ነባራዊ እውነታን አያመለክትም። ወይም በአጭሩ ስለ እውነት የቀረቡ ዘገባዎች እንጂ በራሳቸው እውነት አይደሉም።

  • ሚዲያ እውነታን ይፈጥራል

ሚዲያ መሬት ላይ የሌለ ምናባዊ ዓለም የመፍጠር ዐቅም አለው። አብዛኞቹ አስተሳሰቦቻችን፣ ንጽረተ ዓለሞቻችንና የሕይወት ዘዬዎቻችን ቀጥታ የሚቀዱት ከሚዲያነው።

  • ሚዲያ ለታዳሚው ትርጒም ያቀብላል

እያንዳንዱ ሰው በሚዲያ ከሚተላለፈው ሐሳብ ውስጥ በራሱ ግንዛቤ፣ እምነት፣ ፍላጐትና አተያይ የራሱን ዓለም ይፈጥራል።

  • አብዛኞቹ ሚዲያዎች ትርፍን/ሥልጣንን ታዛቢ ያደረገ ነው

በብዙ መልእክቶች ጀርባ የማትረፍ ግንዛቤ አለ። ስለዚህ የሚተላለፉ መልእክቶች በተቻለ መጠን ብዙ ደንበኞችን የማፍራት ግብን ያነገቡ ናቸው። ትርፍ ከታሰበ አንዳንዴ እውነትን ለድርድር ለማቅረብ የሚገደዱበት ጊዜ ይኖራል። ጥረውን ሐቅ ከማቅረብ ይልቅ ብዙ ታዳሚ ለመሳብ ሲባል ትኲረት የሚስብ ቃላትን ወይም የተጋነኑ አባባሎችን ሊጠቀሙ ይችላሉ።

  • ሚዲያ እሴቶችንና አመለካከቶችን ይይዛሉ

ገለልተኛ የሆነ መልእክት የለም። በሚዲያ የሚተላለፍ ማንኛውም መልእክት የባለቤቱን ወይም የድርጅቱን እሴት ወይም እምነት ለማሰራጨት ጥቅም ላይ የሚውል ነው