KW Innocation & Technology Office

Loading

About Us

About Us

የኮልሜ ወረዳ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ጽሕፈት ቤት ፈጠራን ለማጐልበት፣ የዲጂታል ልውጠት (ትራንስፎርሜሽን) ለማገዝና የእውቀት መር ማኅበረሰብ ለመፍጠር የተቋቋመ መንግሥታዊ ተቋም ነው። ጽሕፈት ቤቱ በዋናነት መንግሥት ለዲጂታል ትራንፎርሜሽን የሰጠውን አገራዊ ራዕይ ለማሳካት የብኲሉን ድርሻ ለማበርከት የተቋቋመ በመሆኑ የማኅበረሰቡን የዲጂታል ክህሎት ለማሳደግ፣ ግንዛቤ ለመጨመርና አዳዲስ የፈጠራና የቴክኖሎጂ ምርቶችን ለማስተዋወቅ አበክሮ ይሠራል። በተለይ ጽሕፈት ቤቱ ወጣቶችን፣ አርሶ አደሮችን፣ ሴቶችን፣ ተማሪዎችን፣ ተቋማትን እና የንግዱን ማኅበረሰብ በዲጂታል ክህሎት የማሳደግ ራዕይ ሰንቆ እየሠራ ይገኛል።

ራዕይ

የኮልሜ ወረዳ ማኅበረሰብ የድኅረ ኢንዱስትሪ ዋና ተዋናይ ሆኖ ማየት!

ተልዕኮዎች

  • ፈጠራ፣ ሳይንስና ቴክኖሎጂን በመጠቀም የማኅበረሰባችን ሕይወት ማቅለል
  • የዜጐችን የዲጂታል ግንዛቤና ክህሎትን ማሳደግ
  • የዲጂታል ሰክተሩ በመጠቀም ሥራ ፈጠራና ኢንተርፕርነየርሺፕ ማሳደግ
  • የክህሎት ሥልጠናዎችን በመስጠት ለሴቶችና ወጣቶች የሥራ ዕድል መፍጠር
  • አዳዲስ የፈጠራ ሥራዎችንና ቴክኖሎጂዎችን ለተቋማት በማስተዋወቅ ቀልጣፋ አገልግሎት መስጠት እንዲችሉ ማድረግ
  • የመረጃ ማጋሪያ አወታሮችን በመጠቀም የማኅበረሰባችንን እሴቶ ማስተዋወቅ
  • ለሰው ሠራሽ አስተውሎት ሞዴሎች ትክክለኛና እውነተኛ መረጃዎችን በማቀበል ማስተማር
  • የዲጂታል አማራጮችን በመጠቀም የቱሪዝም ሰክተሩን ማገዝ

ማዕከላዊ እሴቶች

  • ፈጠራ፡ አዳዲስ ሐሳቦችንና ፈጠራን ማበረታታት
  • ወጥነት፡ በተጠያቂነት መንፈስ ከልብ መሥራት
  • ልህቀት፡ ቀልጣፋና ትክክለኛ አገልግሎት
  • አካታችነት፡ ሁሉን የማኅበረሰብ ክፍሎችን ማቀፍ
  • አብሮ መሥራት፡ ከሁሉም ባለ ድርሻ አካላት ጋር መሥራት
  • የዕድሜ ልክ ተማሪነት፡ ከዘመኑ ጋር አብሮ የሚራመድ እውቀትና ክህሎት
  • ቀጣይነት፡ ለሚመጣው ትውልድ ወረት ማስቀመጥ

የትኲረት መስኮች

  1. ትምህርት
  2. ግብርና
  3. ንግድ
  4. ጤና

ዓላማዎች

ጽሕፈት ቤቱ የተሰጠውን ኃላፊነትና ተግባር ማለትም በወረዳው ዘመናዊ የሆኑ ቴክኖሎጂዎችን በመመርመር፣ በመቅዳት፣ በማላመድና ያለዉን ዐቅም አማጦ ለመጠቀም የሚያስችል የሳይንስና ቴክኖሎጂ መሠረተ ልማቶችን በመዘርጋትና በማስፋፋት የ10 ዓመቱ የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ግብ እንዲሳካ ማድረግ።

Kolme Woreda Innovation and Technology Department is a government institution established to promote innovation, digital transformation, and modern knowledge-based development in Kolme Woreda. The department works to transform society from a traditional agriculture-based economy into a modern economy driven by knowledge, technology, entrepreneurship, and service industries.

We believe that sustainable development comes through education, innovation, creativity, and the effective use of technology. Therefore, our office is committed to building a skilled, informed, and productive community that can compete in the modern world while preserving local culture and resources.

The department supports youth, farmers, women, students, institutions, and businesses through technology awareness, digital literacy, training programs, innovation centers, research support, and entrepreneurship development. By connecting local potential with modern opportunities, we aim to create a prosperous and self-reliant society.

Vision

To make Kolme Woreda a leading knowledge-based and technology-driven society with strong service industries and sustainable economic growth.

Mission

  • To promote innovation, science, and technology for community development.
  • To improve digital literacy and modern skills among citizens.
  • To support entrepreneurship and job creation in the service sector.
  • To modernize agriculture through smart technologies and research.
  • To create opportunities for youth and women through training and innovation.
  • To strengthen institutions through digital systems and efficient services.

Core Values

  • Innovation – Encouraging creativity and new ideas.
  • Integrity – Serving with honesty and accountability.
  • Excellence – Delivering quality and effective services.
  • Inclusiveness – Ensuring participation of all community groups.
  • Collaboration – Working together with stakeholders and partners.
  • Learning – Promoting continuous improvement and knowledge sharing.
  • Sustainability – Protecting resources for future generations.